am_tw/bible/names/phinehas.md

10 lines
1.0 KiB
Markdown

# ፊንሐስ
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ፊንሐስ ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች አሉ።
* አንዱ ፊንሐስ የአሮን የልጅ ልጅና በእስራኤል ሐሰተኛ አማልክት መመለክን አጥብቆ ይቃወም የነበረው ካህን ነበር።
* ምድያማውያን ሴቶች ጋር በመጋባታቸውና ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውንም በማምለካቸው እነርሱን ለመቅጣት ያህዌ ከላከው መቅሠፍት እስራኤልን ያዳነ ፊንሐስ ነበር።
* በተለያየ ጊዜ ፊንሐስ ምድያማውያንን ለማጥፋት ከእስራኤል ሰራዊት ጋር ሄዷል።
* ፊንሐስ ተብሎ የተጠራው ሌላው ሰው በነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ከነበረው ካህኑ ዔሊ ክፉ ልጆች አንድ ነበር።
* ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን በጠቁበትና የኪዳኑ ታቦትንም በወሰዱበት ጊዜ ፊንሐስና ወንድሙ ሐፍኒ ተገድለዋል።