# ፊንሐስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ፊንሐስ ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች አሉ። * አንዱ ፊንሐስ የአሮን የልጅ ልጅና በእስራኤል ሐሰተኛ አማልክት መመለክን አጥብቆ ይቃወም የነበረው ካህን ነበር። * ምድያማውያን ሴቶች ጋር በመጋባታቸውና ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውንም በማምለካቸው እነርሱን ለመቅጣት ያህዌ ከላከው መቅሠፍት እስራኤልን ያዳነ ፊንሐስ ነበር። * በተለያየ ጊዜ ፊንሐስ ምድያማውያንን ለማጥፋት ከእስራኤል ሰራዊት ጋር ሄዷል። * ፊንሐስ ተብሎ የተጠራው ሌላው ሰው በነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ከነበረው ካህኑ ዔሊ ክፉ ልጆች አንድ ነበር። * ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን በጠቁበትና የኪዳኑ ታቦትንም በወሰዱበት ጊዜ ፊንሐስና ወንድሙ ሐፍኒ ተገድለዋል።