am_tw/bible/names/paddanaram.md

8 lines
785 B
Markdown

# ፔዳን አራም (ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ)
ፔዳን አራም ወደ ምድረ ከንዓን ከመሄድ በፊት የአብርሃም ቤተሰብ የነበረበት ቦታ ነው።
* የአብርሃም ወንድም የናኮር ቤተሰብ በፔዳን አራም ቀርቶ ነበር። እነርሱ፣ “አረማውያን” በመባል ሲታወቁ ቋንቋቸውም፣ “አራማይክ” ተብሏል።
* የካራን ከተማ የምትገኘው በፔዳን አራም ሲሆን፣ የርብቃ ወንድም ላባን ይኖር የነበረውም እዚያ ነበር።
* ፔዳን አራም የነበረችው የአሁኗ ሶርያ ባለችበት አካባቢ ወይም ደቡብ ምሥራቅ ቱርክ አካባቢ ሊሆን ይችላል።