# ፔዳን አራም (ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ) ፔዳን አራም ወደ ምድረ ከንዓን ከመሄድ በፊት የአብርሃም ቤተሰብ የነበረበት ቦታ ነው። * የአብርሃም ወንድም የናኮር ቤተሰብ በፔዳን አራም ቀርቶ ነበር። እነርሱ፣ “አረማውያን” በመባል ሲታወቁ ቋንቋቸውም፣ “አራማይክ” ተብሏል። * የካራን ከተማ የምትገኘው በፔዳን አራም ሲሆን፣ የርብቃ ወንድም ላባን ይኖር የነበረውም እዚያ ነበር። * ፔዳን አራም የነበረችው የአሁኗ ሶርያ ባለችበት አካባቢ ወይም ደቡብ ምሥራቅ ቱርክ አካባቢ ሊሆን ይችላል።