am_tw/bible/names/lebanon.md

8 lines
1.0 KiB
Markdown

# ሊባኖስ
ሊባኖስ ከእስራኤል በስተ ሰሜን ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ የምትገኝ በጣም የምታምር ተራራማ ቦታ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ይህ አካባቢ ጥቅጥቅ ባሉት ደኖቹም ይታወቅ ነበር።
* የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥሪያ የሚሆን ዝግባ እንጨት እንዲያመጡለት ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሊባኖስ ሠራተኞች ልኮ ነበር።
* የሊባኖስ ጥንታዊ ኗሪዎች ሊንቃውያን የተሰኙት ሕዝብ ሲሆኑ በንግዱ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ የዋሉ መርከቦችን የመሥራት ችሎታ ነበራቸው።
* የጢሮስና የሲዶና ከተሞች ሊባኖስ ውስጥ ነበር። ውድ ዋጋ ያለው ሐምራዊ ቀለም ያለ የተነከረ ጨርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በእነዚህ ከተሞች ነበር።