# ሊባኖስ ሊባኖስ ከእስራኤል በስተ ሰሜን ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ የምትገኝ በጣም የምታምር ተራራማ ቦታ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ይህ አካባቢ ጥቅጥቅ ባሉት ደኖቹም ይታወቅ ነበር። * የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥሪያ የሚሆን ዝግባ እንጨት እንዲያመጡለት ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሊባኖስ ሠራተኞች ልኮ ነበር። * የሊባኖስ ጥንታዊ ኗሪዎች ሊንቃውያን የተሰኙት ሕዝብ ሲሆኑ በንግዱ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ የዋሉ መርከቦችን የመሥራት ችሎታ ነበራቸው። * የጢሮስና የሲዶና ከተሞች ሊባኖስ ውስጥ ነበር። ውድ ዋጋ ያለው ሐምራዊ ቀለም ያለ የተነከረ ጨርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በእነዚህ ከተሞች ነበር።