am_tw/bible/names/hananiah.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown

# አናንያ
ከትንቢተ ዳንኤል እንደምንመለከተው አናንያ በምርኮ ዘመን ወደ ባቢሎን ተወስደው ስለነበሩ አስተዋይ አይሁዳውያን ወጣቶች አንዱ ነበር። ይበልጥ የሚታወቀው ሲድራቅ በተሰኘው ስሙ ነው።
* ባሳየው የፀባይ ብልጫና እግዚአብሔር ከሰጠው ችሎታ የተነሣ ባቢሎናውያን ለአናንያ ከፍተኛ ሥልጣን ሰጥተውት ነበር።
* የባቢሎን ንጉሥ ለአናንያ ሲድራቅ የሚል ስም ሰጠው።
* ለንጉሡ መስገድ ባለ መፈለጋቸው ከሌሎች አይሁዳውያን ጓደኞቹ ጋር ሲድራቅ እሳት ውስጥ ተጥሎ ነበር። እነርሱ ላይ ምንም ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ እግዚአብሔር ኀይሉን አሳየ።
* በተለያዩ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች እናንያ (ሐናንያ) የሚባሉ ይህን ያህል ታዋቂነት ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ።
* አንደኛው አናንያ (ሐናንያ) በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የነበረው ሐሰተኛ ነቢይ ነው።