# አናንያ ከትንቢተ ዳንኤል እንደምንመለከተው አናንያ በምርኮ ዘመን ወደ ባቢሎን ተወስደው ስለነበሩ አስተዋይ አይሁዳውያን ወጣቶች አንዱ ነበር። ይበልጥ የሚታወቀው ሲድራቅ በተሰኘው ስሙ ነው። * ባሳየው የፀባይ ብልጫና እግዚአብሔር ከሰጠው ችሎታ የተነሣ ባቢሎናውያን ለአናንያ ከፍተኛ ሥልጣን ሰጥተውት ነበር። * የባቢሎን ንጉሥ ለአናንያ ሲድራቅ የሚል ስም ሰጠው። * ለንጉሡ መስገድ ባለ መፈለጋቸው ከሌሎች አይሁዳውያን ጓደኞቹ ጋር ሲድራቅ እሳት ውስጥ ተጥሎ ነበር። እነርሱ ላይ ምንም ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ እግዚአብሔር ኀይሉን አሳየ። * በተለያዩ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች እናንያ (ሐናንያ) የሚባሉ ይህን ያህል ታዋቂነት ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ። * አንደኛው አናንያ (ሐናንያ) በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የነበረው ሐሰተኛ ነቢይ ነው።