am_tw/bible/names/gaza.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown

# ጋዛ
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጋዛ የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ፣ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ 77 ኪሎ ሜትር፣ ከአሽዶድ በስተ ሰሜን 38 ኪሎ ሜትር ላይ ትገኝ የነበረች በጣም አስፈላጊ የፍልስጥኤማውያን ከተማ ነበረች።
* በጥንት ዘመን ጋዛ በእስያና በግብፅ መሐል ያለች የወታደራዊና የንግድ መተላለፊያ በር ነበረች።
* በዚህ ዘመንም ጋዛ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ወደብ ስትሆን፣ ሜዴትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ የምትገኝና በስተ ሰሜንና በስተ ምሥራቅ ከእስራኤል ጋር፣ በስተ ደቡብ ከግብፅ ጋር ትዋሰናለች።
* ፍልስጥኤማውያን ሳምሶንን ከያዙት በኋላ የወሰዱት ወደ ጋዛ ነበር።
* ወንጌላዊው ፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ያገኘው ወደ ጋዛ በሚወስደው የበረሐ መንገድ ላይ ነበር።