# ጋዛ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጋዛ የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ፣ ከኢየሩሳሌም ደቡብ ምዕራብ 77 ኪሎ ሜትር፣ ከአሽዶድ በስተ ሰሜን 38 ኪሎ ሜትር ላይ ትገኝ የነበረች በጣም አስፈላጊ የፍልስጥኤማውያን ከተማ ነበረች። * በጥንት ዘመን ጋዛ በእስያና በግብፅ መሐል ያለች የወታደራዊና የንግድ መተላለፊያ በር ነበረች። * በዚህ ዘመንም ጋዛ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ወደብ ስትሆን፣ ሜዴትራንያን ባሕር ዳርቻ አካባቢ የምትገኝና በስተ ሰሜንና በስተ ምሥራቅ ከእስራኤል ጋር፣ በስተ ደቡብ ከግብፅ ጋር ትዋሰናለች። * ፍልስጥኤማውያን ሳምሶንን ከያዙት በኋላ የወሰዱት ወደ ጋዛ ነበር። * ወንጌላዊው ፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ያገኘው ወደ ጋዛ በሚወስደው የበረሐ መንገድ ላይ ነበር።