am_tw/bible/names/gath.md

8 lines
871 B
Markdown

# ጌት
ጌት ከአምስቱ የፍልስጥኤም ዋና ዋና ከተሞች አንዷ ነበረች። የምትገኘው ከአቃሮን በስተ ሰሜንና ከአሾዶድና ከአስቄሎና በስተ ምሥራቅ ነበር።
* የፍልስጥኤማውያን ጀግና ጎልያድ አገር ጌት ነበር።
* በሳሙኤል ዘመን ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከእስራኤል ዘርፈው አአሽደድ ወደ ነበረው የአረማውያን ቤተ መቅደስ ከዚያም ወደ ጌት ወስደውት ነበር። ሆኖም. እግዚአብሔር የነዚህ ከተሞችን ሰዎች በበሽታ በመቅጣቱ፣ ወደ እስራኤል መለሱት።
* ዳዊት ከንጉሥ ሳኦል በሸሸ ጊዜ ወደ ጌት ሄዶ ከሁለት ሚስቶቹ ጋር ለአጭር ጊዜ እዚያ ኖረ።