# ጌት ጌት ከአምስቱ የፍልስጥኤም ዋና ዋና ከተሞች አንዷ ነበረች። የምትገኘው ከአቃሮን በስተ ሰሜንና ከአሾዶድና ከአስቄሎና በስተ ምሥራቅ ነበር። * የፍልስጥኤማውያን ጀግና ጎልያድ አገር ጌት ነበር። * በሳሙኤል ዘመን ፍልስጥኤማውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከእስራኤል ዘርፈው አአሽደድ ወደ ነበረው የአረማውያን ቤተ መቅደስ ከዚያም ወደ ጌት ወስደውት ነበር። ሆኖም. እግዚአብሔር የነዚህ ከተሞችን ሰዎች በበሽታ በመቅጣቱ፣ ወደ እስራኤል መለሱት። * ዳዊት ከንጉሥ ሳኦል በሸሸ ጊዜ ወደ ጌት ሄዶ ከሁለት ሚስቶቹ ጋር ለአጭር ጊዜ እዚያ ኖረ።