am_tw/bible/names/euphrates.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown

# ኤፍራጥስ
ኤፍራጥስ በኤደን የአትክልት ቦታ ውስጥ ያልፉ ከነበሩ አራት ወንዞች አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሰ ወንዝ ነው፣ አንዳንዴ፣ “ወንዙ” በመባል በአጭር ቃል ተጠርቷል።
* በዚህ ዘመን ኤፍራጥስ ተብሎ የሚጠራው ወንዝ የሚገኘው መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ሲሆን፣ በእስያ ካሉት ወንዞች ረጅሙና በጣም ጠቃሚው ወንዝ ነው።
* ከጤግሮስ ወንዝ ጋር በአንድነት ኤፍራጥስ ሜስፖታሚያ በመባል ከሚታወቀው ምድር ጋር ይዋሰናል።
* አብርሃም የተገኘባት የጥንቷ ዑር ከተማ የምትገኘው የኤፍራጥስ ወንዝ ልሳን ላይ ነበር።
* ይህ ወንዝ ለአብርሃም እንደሚሰጠው እግዚአብሔር ቃል የገባለት ምድር ድንበሮች አንዱ ነው። (ዘፍጥረት 15፣18)