# ኤፍራጥስ ኤፍራጥስ በኤደን የአትክልት ቦታ ውስጥ ያልፉ ከነበሩ አራት ወንዞች አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሰ ወንዝ ነው፣ አንዳንዴ፣ “ወንዙ” በመባል በአጭር ቃል ተጠርቷል። * በዚህ ዘመን ኤፍራጥስ ተብሎ የሚጠራው ወንዝ የሚገኘው መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ሲሆን፣ በእስያ ካሉት ወንዞች ረጅሙና በጣም ጠቃሚው ወንዝ ነው። * ከጤግሮስ ወንዝ ጋር በአንድነት ኤፍራጥስ ሜስፖታሚያ በመባል ከሚታወቀው ምድር ጋር ይዋሰናል። * አብርሃም የተገኘባት የጥንቷ ዑር ከተማ የምትገኘው የኤፍራጥስ ወንዝ ልሳን ላይ ነበር። * ይህ ወንዝ ለአብርሃም እንደሚሰጠው እግዚአብሔር ቃል የገባለት ምድር ድንበሮች አንዱ ነው። (ዘፍጥረት 15፣18)