am_tw/bible/names/ethiopia.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown

# ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ
ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ ያለች አፍሪካዊት አገር ስትሆን፣ በስተምዕራብ የአባይ ወንዝ፣ በስተምሥራቅ ደግሞ ከቀይ ባሕር ጋር ትዋሰናለች። ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘ ሰው ኢትዮጵያዊ ይባላል።
* የጥንቷ ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ ያለች ሱዳንን፣ የአሁኗ ኢትዮጵያን፣ ሶማልያን፣ ኬንያን፣ ዩጋንዳን፣ ማዕከላዊ ሪፖብሊክንና ቻድን የመሳሰሉ በርካታ የዘመኑ አፍሪካ አገሮችን የምታካትት ነበረች።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢትዮጵያ አንዳንዴ “ኩሽ” ወይም፣ “ኑቢያ” ትባላለች።
* የኢትዮጵያ አገሮች (“ኩሽ”) እና ግብፅ ብዙ ጊዜ በአንድነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል፤ እንዲህ የሆነው ጎረቤታሞች ስለሆኑና ሕዝቦቻቸው ተመሳሳይ ጥንተአባቶች ስለነበሯቸው ሊሆን ይችላል።
* እግዚአብሔር ፊልጶስን ወደምድረ በዳ ላከው፣ እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥራች ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ተናገረ።