# ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ ያለች አፍሪካዊት አገር ስትሆን፣ በስተምዕራብ የአባይ ወንዝ፣ በስተምሥራቅ ደግሞ ከቀይ ባሕር ጋር ትዋሰናለች። ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘ ሰው ኢትዮጵያዊ ይባላል። * የጥንቷ ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ ያለች ሱዳንን፣ የአሁኗ ኢትዮጵያን፣ ሶማልያን፣ ኬንያን፣ ዩጋንዳን፣ ማዕከላዊ ሪፖብሊክንና ቻድን የመሳሰሉ በርካታ የዘመኑ አፍሪካ አገሮችን የምታካትት ነበረች። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢትዮጵያ አንዳንዴ “ኩሽ” ወይም፣ “ኑቢያ” ትባላለች። * የኢትዮጵያ አገሮች (“ኩሽ”) እና ግብፅ ብዙ ጊዜ በአንድነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል፤ እንዲህ የሆነው ጎረቤታሞች ስለሆኑና ሕዝቦቻቸው ተመሳሳይ ጥንተአባቶች ስለነበሯቸው ሊሆን ይችላል። * እግዚአብሔር ፊልጶስን ወደምድረ በዳ ላከው፣ እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥራች ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ተናገረ።