am_tw/bible/names/esther.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown

# አስቴር
አይሁድ በባቢሎን በምርኮ በነበሩበት ዘመን የፋርስ መንግሥት ልዕልት የሆነች አይሁዳዊት ሴት ናት።
* አስቴር የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ልዕልት መሆን እንዴት እንደቻለችና ሕዝቧን ለማዳን እግዚአብሔር እንደተጠቀመባት መጽሐፈ አስቴር ይናገራል።
* አስቴር አባትና እናት ያልነበራት ስትሆን፣ ያሳደጋት እግዚአብሔርን የሚፈራው ሽማግሌው አጎቷ መርዶክዮስ ነበር።
* ለአሳዳጊ አባቷ ታዛዥ መሆንዋ፣ ለእግዚአብሔርም ታዛዥ እንድትሆን ረዳት።
* ሕዝቧ አይሁድን ለማዳን ስትል ሕይወቷን ለአደጋ በማጋለጥ አስቴር ለእግዚአብሔር ታዝዛለች።
* መጽሐፈ አስቴር በታሪክ ውስጥ የሚፈጸሙ ነገሮችን ለመቆጣጠር የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነትና በተለይም እንዴት ሕዝቡን እንደሚጠብቅና ለእርሱ በሚታዘዙ ሰዎች በኩል እንዴት እንደሚሠራ ይገልጻል።