1.2 KiB
1.2 KiB
አስቴር
አይሁድ በባቢሎን በምርኮ በነበሩበት ዘመን የፋርስ መንግሥት ልዕልት የሆነች አይሁዳዊት ሴት ናት።
- አስቴር የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ልዕልት መሆን እንዴት እንደቻለችና ሕዝቧን ለማዳን እግዚአብሔር እንደተጠቀመባት መጽሐፈ አስቴር ይናገራል።
- አስቴር አባትና እናት ያልነበራት ስትሆን፣ ያሳደጋት እግዚአብሔርን የሚፈራው ሽማግሌው አጎቷ መርዶክዮስ ነበር።
- ለአሳዳጊ አባቷ ታዛዥ መሆንዋ፣ ለእግዚአብሔርም ታዛዥ እንድትሆን ረዳት።
- ሕዝቧ አይሁድን ለማዳን ስትል ሕይወቷን ለአደጋ በማጋለጥ አስቴር ለእግዚአብሔር ታዝዛለች።
- መጽሐፈ አስቴር በታሪክ ውስጥ የሚፈጸሙ ነገሮችን ለመቆጣጠር የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነትና በተለይም እንዴት ሕዝቡን እንደሚጠብቅና ለእርሱ በሚታዘዙ ሰዎች በኩል እንዴት እንደሚሠራ ይገልጻል።