am_tw/bible/names/david.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ዳዊት
ዳዊት እግዚአብሔርን በመውደዱና እርሱን በማገልገሉ የታወቀ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ ነው። የመዝሙራት መጽሐፍ ዋናው ጸሐፊም እርሱ ነው።
* ዳዊት ገና ትንሽ ልጅ እያለ የቤተ ሰቡን በጎች ሲጠብቅ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው።
* ዳዊት ብርቱ ጦረኛ ሆነ፤ በጠላቶቻቸው ላይ እንዲዘምቱ የእስራኤልን ሰራዊት መርቷል። ፍልስጥኤማዊው ጎልያድን ማሸነፉ በጣም ታዋቂ እንዲሆን አድርጎታል።
* ንጉሥ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ሞክሮ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እርስን ጠብቀው፤ ከሳኦል ሞት በኋላም ንጉሥ አደረገው።
* ዳዊት በጣም ከባድ ኀጢአት ፈጽሞ ነበር፤ ይሁን እንጂ ንስሐ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ይቅር አለው።
* የንጉሥ ዳዊት ዘር በመሆኑ መሲሑ ኢየሱስ፣ “የዳዊት ልጅ” ተብሏል።