# ዳዊት ዳዊት እግዚአብሔርን በመውደዱና እርሱን በማገልገሉ የታወቀ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ ነው። የመዝሙራት መጽሐፍ ዋናው ጸሐፊም እርሱ ነው። * ዳዊት ገና ትንሽ ልጅ እያለ የቤተ ሰቡን በጎች ሲጠብቅ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እግዚአብሔር መረጠው። * ዳዊት ብርቱ ጦረኛ ሆነ፤ በጠላቶቻቸው ላይ እንዲዘምቱ የእስራኤልን ሰራዊት መርቷል። ፍልስጥኤማዊው ጎልያድን ማሸነፉ በጣም ታዋቂ እንዲሆን አድርጎታል። * ንጉሥ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ሞክሮ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እርስን ጠብቀው፤ ከሳኦል ሞት በኋላም ንጉሥ አደረገው። * ዳዊት በጣም ከባድ ኀጢአት ፈጽሞ ነበር፤ ይሁን እንጂ ንስሐ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ይቅር አለው። * የንጉሥ ዳዊት ዘር በመሆኑ መሲሑ ኢየሱስ፣ “የዳዊት ልጅ” ተብሏል።