am_tw/bible/names/canaan.md

8 lines
858 B
Markdown

# ከነዓን፣ ከነዓናዊ
ከነዓን የኖኅ ወንዶች ልጆች አንዱ የነበረው የካም ልጅ ነበር። ከነዓናውያን የከነዓን ዘሮች ናቸው።
* “ከነዓን” ወይም “የከነዓን ምድር” የሚለው ቃል በዮርዳኖስ ወንዝና በሜዲትራንያን ባሕር መካከል የነበረውንም ቦታ ወይም አካባቢ ያመልክታል። በስተ ደቡብ በኩል እስክ ግብፅ ዳርቻና በስተ ሰሜን እስከ ሶርያ ዳርቻ ይደርሳል።
* በዚያ ምድር ከንዓናውያንና ሌሎችም በርካታ ሕዝቦች ይኖሩ ነበር።
* የከነዓንን ምድር ለአብርሃምና የእርሱ ዘሮች ለሆኑት እስራኤላውያን እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶአል።