# ከነዓን፣ ከነዓናዊ ከነዓን የኖኅ ወንዶች ልጆች አንዱ የነበረው የካም ልጅ ነበር። ከነዓናውያን የከነዓን ዘሮች ናቸው። * “ከነዓን” ወይም “የከነዓን ምድር” የሚለው ቃል በዮርዳኖስ ወንዝና በሜዲትራንያን ባሕር መካከል የነበረውንም ቦታ ወይም አካባቢ ያመልክታል። በስተ ደቡብ በኩል እስክ ግብፅ ዳርቻና በስተ ሰሜን እስከ ሶርያ ዳርቻ ይደርሳል። * በዚያ ምድር ከንዓናውያንና ሌሎችም በርካታ ሕዝቦች ይኖሩ ነበር። * የከነዓንን ምድር ለአብርሃምና የእርሱ ዘሮች ለሆኑት እስራኤላውያን እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶአል።