am_tw/bible/kt/wrath.md

768 B

መዓት፣ ቁጣ

መዓት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በጣም ከባድ ቁጣ ነው። ብዙውን ጊዜ ኀጢአት ላይ የሚመጣውን የእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድና በእርሱ ላይ የሚያምፁ ሰዎችን ቅጣት ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መዓት” ብዙውን ጊዜ እርሱ ላይ ኀጢአት በሚያደርጉት ሰዎች የሚመጣውን የእግዚአብሔር ቁጣ ያመለክታል።
  • የእግዚአብሔር “መዓት” ኀጢአት ላይ መፍረዱንና መቅጣቱንም ያመለክታል።
  • የእግዚአብሔር መዓት ከኀጢአታቸው በንስሐ ለማይመለሱ ሰዎች የሚገባ የጽድቅ ቅጣት ነው።