# መዓት፣ ቁጣ መዓት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ በጣም ከባድ ቁጣ ነው። ብዙውን ጊዜ ኀጢአት ላይ የሚመጣውን የእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድና በእርሱ ላይ የሚያምፁ ሰዎችን ቅጣት ያመለክታል። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መዓት” ብዙውን ጊዜ እርሱ ላይ ኀጢአት በሚያደርጉት ሰዎች የሚመጣውን የእግዚአብሔር ቁጣ ያመለክታል። * የእግዚአብሔር “መዓት” ኀጢአት ላይ መፍረዱንና መቅጣቱንም ያመለክታል። * የእግዚአብሔር መዓት ከኀጢአታቸው በንስሐ ለማይመለሱ ሰዎች የሚገባ የጽድቅ ቅጣት ነው።