am_tw/bible/kt/worthy.md

1.1 KiB

የሚገባው፣ ዋጋ ያለው፣ የማይገባው፣ ዋጋ ቢስ

“የሚገባው” የሚለው ቃል ክብርና ምስጋና መቀበል ያለበትን ያመለክታል። “ዋጋ ያለው” ውድ ወይም ጠቃሚ ነገርን ያመለክታል። “ዋጋ ቢስ” ግን ለምንም የማይጠቅም ማለት ነው።

  • የሚገባው የሚለው ዋጋ ወይም ጥቅም ያለው ከሚለው ጋር ይያያዛል።
  • “የማይገባው” ምንም ዓይነት ትኵረት ሊሰጠው የማይበቃ ማለት ነው።
  • ራስን እንደ ዋጋ ቢስ መቁጠር ለራስ ዝቅ ያለ ግምት መስጠት፣ ክብርና ችሮታ ላደረገለት ብቁ እንዳልሆነ ሰው መቁጠር ማለት ነው።
  • “የማይገባው” እና፣ “ዋጋ ቢስ” የተሰኙት ቢቀራረቡም ልዩነት አላቸው። “የማይገባው”ምንም ዓይነት ክብርና ዕውቅና ሊሰጠው የማይገባ ማለት ነው። “ዋጋ ቢስ” ግን ዓላማም ሆነ ጠቀሜታ የሌለው ማለት ነው።