# የሚገባው፣ ዋጋ ያለው፣ የማይገባው፣ ዋጋ ቢስ “የሚገባው” የሚለው ቃል ክብርና ምስጋና መቀበል ያለበትን ያመለክታል። “ዋጋ ያለው” ውድ ወይም ጠቃሚ ነገርን ያመለክታል። “ዋጋ ቢስ” ግን ለምንም የማይጠቅም ማለት ነው። * የሚገባው የሚለው ዋጋ ወይም ጥቅም ያለው ከሚለው ጋር ይያያዛል። * “የማይገባው” ምንም ዓይነት ትኵረት ሊሰጠው የማይበቃ ማለት ነው። * ራስን እንደ ዋጋ ቢስ መቁጠር ለራስ ዝቅ ያለ ግምት መስጠት፣ ክብርና ችሮታ ላደረገለት ብቁ እንዳልሆነ ሰው መቁጠር ማለት ነው። * “የማይገባው” እና፣ “ዋጋ ቢስ” የተሰኙት ቢቀራረቡም ልዩነት አላቸው። “የማይገባው”ምንም ዓይነት ክብርና ዕውቅና ሊሰጠው የማይገባ ማለት ነው። “ዋጋ ቢስ” ግን ዓላማም ሆነ ጠቀሜታ የሌለው ማለት ነው።