am_tw/bible/kt/woe.md

8 lines
644 B
Markdown

# ወዮ
“ወዮ” ከፍ ያለ ጭንቀትና ሐዘንን ያመለክታል። ስለሚመጣው ከባድ ጥፋት ማስጠንቀቂያም ይሆናል።
* “ለ. . . ወዮ” ማለት ለኀጢአታቸው ቅጣት እንዲሆን ሰዎች ላይ የሚወርድ ከባድ መከራን ያመለክታል።
* በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለሚመጣው ከባድ ፍርድ አጽንዖት ለመስጠት፣ “ወዮ” የሚለው ቃል ተደጋግሞአል።
* “ወዮልኝ” የሚል ሰው ከከባድ መከራ የተነሣ የደረሰበትን ሐዘን መግለጹ ነው።