# ወዮ “ወዮ” ከፍ ያለ ጭንቀትና ሐዘንን ያመለክታል። ስለሚመጣው ከባድ ጥፋት ማስጠንቀቂያም ይሆናል። * “ለ. . . ወዮ” ማለት ለኀጢአታቸው ቅጣት እንዲሆን ሰዎች ላይ የሚወርድ ከባድ መከራን ያመለክታል። * በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለሚመጣው ከባድ ፍርድ አጽንዖት ለመስጠት፣ “ወዮ” የሚለው ቃል ተደጋግሞአል። * “ወዮልኝ” የሚል ሰው ከከባድ መከራ የተነሣ የደረሰበትን ሐዘን መግለጹ ነው።