am_tw/bible/kt/true.md

10 lines
1.0 KiB
Markdown

# እውነት፣ እውነተኛ
“እውነት” የሚለው ቃል ይተረጋገጠ ፅንሰ ሐሳብን፣ በትክክል የተፈጸመ ሁኔታንና በእርግጥ የተነገረ ቃልን ያመለክታል።
* እውነተኛ ነገሮች፣ እውን የሆኑ፣ ትክክለኛ፣ እርግጠኛ፣ ተገቢ፣ ሕጋዊና አግባብ የሆኑ ነገሮች ናቸው።
* እምነትን፣ ሐቅን ወይም እውነት የሆነውን መረዳት እውነተኛ መሆን ነው።
* አስተማማኝና እርግጠኛ በሆነ መልኩ መንቀሳቀስን የሚያመለክት ፅንሰ ሐሳብ እውነተኛነትን ያመለክታል።
* ኢየሱስ በተናገረው ሁሉ የእግዚአብሔርን እውነት ገልጧል።
* የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው። በትክክል የተፈጸመ ነገርን ይናገራል፤ ስለ እግዚአብሔርና እርሱ ስለ ፈጠራቸው ማንኛውም ነገሮች እውንቱን ያስተምራል።