# እውነት፣ እውነተኛ “እውነት” የሚለው ቃል ይተረጋገጠ ፅንሰ ሐሳብን፣ በትክክል የተፈጸመ ሁኔታንና በእርግጥ የተነገረ ቃልን ያመለክታል። * እውነተኛ ነገሮች፣ እውን የሆኑ፣ ትክክለኛ፣ እርግጠኛ፣ ተገቢ፣ ሕጋዊና አግባብ የሆኑ ነገሮች ናቸው። * እምነትን፣ ሐቅን ወይም እውነት የሆነውን መረዳት እውነተኛ መሆን ነው። * አስተማማኝና እርግጠኛ በሆነ መልኩ መንቀሳቀስን የሚያመለክት ፅንሰ ሐሳብ እውነተኛነትን ያመለክታል። * ኢየሱስ በተናገረው ሁሉ የእግዚአብሔርን እውነት ገልጧል። * የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው። በትክክል የተፈጸመ ነገርን ይናገራል፤ ስለ እግዚአብሔርና እርሱ ስለ ፈጠራቸው ማንኛውም ነገሮች እውንቱን ያስተምራል።