am_tw/bible/kt/true.md

1.0 KiB

እውነት፣ እውነተኛ

“እውነት” የሚለው ቃል ይተረጋገጠ ፅንሰ ሐሳብን፣ በትክክል የተፈጸመ ሁኔታንና በእርግጥ የተነገረ ቃልን ያመለክታል።

  • እውነተኛ ነገሮች፣ እውን የሆኑ፣ ትክክለኛ፣ እርግጠኛ፣ ተገቢ፣ ሕጋዊና አግባብ የሆኑ ነገሮች ናቸው።
  • እምነትን፣ ሐቅን ወይም እውነት የሆነውን መረዳት እውነተኛ መሆን ነው።
  • አስተማማኝና እርግጠኛ በሆነ መልኩ መንቀሳቀስን የሚያመለክት ፅንሰ ሐሳብ እውነተኛነትን ያመለክታል።
  • ኢየሱስ በተናገረው ሁሉ የእግዚአብሔርን እውነት ገልጧል።
  • የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው። በትክክል የተፈጸመ ነገርን ይናገራል፤ ስለ እግዚአብሔርና እርሱ ስለ ፈጠራቸው ማንኛውም ነገሮች እውንቱን ያስተምራል።