am_tw/bible/kt/testimony.md

890 B

ምስክር፣ መመስከር

“ምስክር” እና፣ “መመስከር” አንድን ነገር በተመለከተ የሚያውቁትን እውነት በግልጽና በሰው ሁሉ ፊት መናገር ማለት ነው።

  • ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው፣ “የሚመሰክረው” በትክክል ስለሚያውቀውና በቀጥታ ስለ ተለማመደው ነገር ነው።
  • ሐሰት የሚናገር “ምስክር” የተፈጸመውን ነገር አስመልክቶ እውነቱን እየተናገረ አይደለም።
  • አንዳንዴ፣ “ምስክር” ነቢይ የተናገረውን ትንቢት ያመለክታል።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ይህ ቃል የሚያመለክተው የኢየሱስ ተከታዮች ስለ እርሱ ሕይወት፣ ሞትና ትንሣኤ የሚናገሩትን ሁሉ ነው።