am_tw/bible/kt/testimony.md

9 lines
890 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ምስክር፣ መመስከር
“ምስክር” እና፣ “መመስከር” አንድን ነገር በተመለከተ የሚያውቁትን እውነት በግልጽና በሰው ሁሉ ፊት መናገር ማለት ነው።
* ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው፣ “የሚመሰክረው” በትክክል ስለሚያውቀውና በቀጥታ ስለ ተለማመደው ነገር ነው።
* ሐሰት የሚናገር “ምስክር” የተፈጸመውን ነገር አስመልክቶ እውነቱን እየተናገረ አይደለም።
* አንዳንዴ፣ “ምስክር” ነቢይ የተናገረውን ትንቢት ያመለክታል።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ይህ ቃል የሚያመለክተው የኢየሱስ ተከታዮች ስለ እርሱ ሕይወት፣ ሞትና ትንሣኤ የሚናገሩትን ሁሉ ነው።