# ምስክር፣ መመስከር “ምስክር” እና፣ “መመስከር” አንድን ነገር በተመለከተ የሚያውቁትን እውነት በግልጽና በሰው ሁሉ ፊት መናገር ማለት ነው። * ብዙውን ጊዜ አንድ ሰው፣ “የሚመሰክረው” በትክክል ስለሚያውቀውና በቀጥታ ስለ ተለማመደው ነገር ነው። * ሐሰት የሚናገር “ምስክር” የተፈጸመውን ነገር አስመልክቶ እውነቱን እየተናገረ አይደለም። * አንዳንዴ፣ “ምስክር” ነቢይ የተናገረውን ትንቢት ያመለክታል። * አዲስ ኪዳን ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ይህ ቃል የሚያመለክተው የኢየሱስ ተከታዮች ስለ እርሱ ሕይወት፣ ሞትና ትንሣኤ የሚናገሩትን ሁሉ ነው።