am_tw/bible/kt/test.md

1.5 KiB

ፈተና

“ፈተና” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ብርታትና ድካም ለይቶ የሚያሳይ አስቸጋሪ ወይም አዳጋች ሁኔታ ያመለክታል።

  • የሰዎችን ኀጢአት ለመግለጥ አንዳንዴ እግዚአብሔር በሚመጡ ፈተናዎች ይጠቀማል። ፈተና ሰዎች ከኀጢአት እንዲመለሱና ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ ይረዳል።
  • ምን ያህል ንጹሕ ወይም ጠንካራ መሆናቸውን ለመለየት ወርቅና ሌሎች የብረት ዐይነቶች በእሳት ይፈተናሉ። ይህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመፈተን አዳጋችና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንደሚጠቀም የሚያመለክት ሥዕል ነው።
  • እግዚአብሔር ሰዎችን ይፈትናል፤ ይሁን እንጂ ኀጢአት እንዲያደርጉ ምክንያት የሚሆን ፈተና አያመጣባቸውም፤ ሰይጣን ሰዎችን የሚፈትነው ኀጢአት እንዲፈጽሙ ለማድረግ ነ።ው
  • “መፈተን” የአንድ ሰው ወይም ነገር ትክክለኛ ምንነት ይፋ እንዲወጣ መገዳደር” ማለት ነው።
  • እግዚአብሔርን መፈተን ባለ መታዘዝ መጽናት፣ ለምሕረቱ ዋጋ አለመስጠት ማለት ነው።
  • እግዚአብሔርን መፈተን እንደማይገባ ኢየሱስ ለሰይጣን ነግሮታል። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ ቅዱስና ከማንኛውም ነገር በላይ ነው።