am_tw/bible/kt/test.md

11 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ፈተና
“ፈተና” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ብርታትና ድካም ለይቶ የሚያሳይ አስቸጋሪ ወይም አዳጋች ሁኔታ ያመለክታል።
* የሰዎችን ኀጢአት ለመግለጥ አንዳንዴ እግዚአብሔር በሚመጡ ፈተናዎች ይጠቀማል። ፈተና ሰዎች ከኀጢአት እንዲመለሱና ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ ይረዳል።
* ምን ያህል ንጹሕ ወይም ጠንካራ መሆናቸውን ለመለየት ወርቅና ሌሎች የብረት ዐይነቶች በእሳት ይፈተናሉ። ይህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመፈተን አዳጋችና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንደሚጠቀም የሚያመለክት ሥዕል ነው።
* እግዚአብሔር ሰዎችን ይፈትናል፤ ይሁን እንጂ ኀጢአት እንዲያደርጉ ምክንያት የሚሆን ፈተና አያመጣባቸውም፤ ሰይጣን ሰዎችን የሚፈትነው ኀጢአት እንዲፈጽሙ ለማድረግ ነ።ው
* “መፈተን” የአንድ ሰው ወይም ነገር ትክክለኛ ምንነት ይፋ እንዲወጣ መገዳደር” ማለት ነው።
* እግዚአብሔርን መፈተን ባለ መታዘዝ መጽናት፣ ለምሕረቱ ዋጋ አለመስጠት ማለት ነው።
* እግዚአብሔርን መፈተን እንደማይገባ ኢየሱስ ለሰይጣን ነግሮታል። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ ቅዱስና ከማንኛውም ነገር በላይ ነው።