# ፈተና “ፈተና” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ብርታትና ድካም ለይቶ የሚያሳይ አስቸጋሪ ወይም አዳጋች ሁኔታ ያመለክታል። * የሰዎችን ኀጢአት ለመግለጥ አንዳንዴ እግዚአብሔር በሚመጡ ፈተናዎች ይጠቀማል። ፈተና ሰዎች ከኀጢአት እንዲመለሱና ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ ይረዳል። * ምን ያህል ንጹሕ ወይም ጠንካራ መሆናቸውን ለመለየት ወርቅና ሌሎች የብረት ዐይነቶች በእሳት ይፈተናሉ። ይህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመፈተን አዳጋችና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንደሚጠቀም የሚያመለክት ሥዕል ነው። * እግዚአብሔር ሰዎችን ይፈትናል፤ ይሁን እንጂ ኀጢአት እንዲያደርጉ ምክንያት የሚሆን ፈተና አያመጣባቸውም፤ ሰይጣን ሰዎችን የሚፈትነው ኀጢአት እንዲፈጽሙ ለማድረግ ነ።ው * “መፈተን” የአንድ ሰው ወይም ነገር ትክክለኛ ምንነት ይፋ እንዲወጣ መገዳደር” ማለት ነው። * እግዚአብሔርን መፈተን ባለ መታዘዝ መጽናት፣ ለምሕረቱ ዋጋ አለመስጠት ማለት ነው። * እግዚአብሔርን መፈተን እንደማይገባ ኢየሱስ ለሰይጣን ነግሮታል። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ ቅዱስና ከማንኛውም ነገር በላይ ነው።