am_tw/bible/kt/sign.md

1.5 KiB

ምልክት፥ ማረጋገጫ፣ ማሳሰቢያ

ምልክት የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት የሚያስተላልፍ ዕቃ፣ ሁኔታ ወይም ድርጊት ሊሆን ይችላል

  • ምልክቶች ቃል ለተገባለት ነገር እንደ ማሳሰቢያ ያገለግላል
  • ሰማይ ላይ የምናየው ቀስተ ደመና ከእንግዲህ በምድር ሁሉ ላይ በሚሆን ጎርፍ ሕይወትን ሁሉ እንደማያጠፋ የሚያሳስብ ምልክት ነው
  • ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዲሆን ልጆቻቸውን እንዲገርዙ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ
  • ምልክቶች አንድን ነገር ይገልጣሉ ወይም ያመለክታሉ
  • በቤተ ልሔም አዲስ የተወለደው መሲህ የትኛው ሕፃን መሆኑን ማወቅ እንዲችሉ መልአኩ ለእረኞቹ ምልክት ነገራቸው
  • ማሰር ያለባቸው እርሱን እንደሆነ ለአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ለማሳየት ምልክት እንዲሆን ይሁዳ ኢየሱስን ሳመ
  • ምልክቶች አንድ ነገር እውነት መሆኑን ሊያመለክቱ ይችላሉ
  • ነቢያትና ሐዋርያት የደረጓቸው ተአምራት የተናገሩት የእግዚአብሔርን መልእክት መሆኑን የሚያረጋግጡ ምልክቶች ነበሩ
  • ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት እርሱ በእውነት መሲሕ ለመሆኑ፣ ምልክቶች ናቸው