# ምልክት፥ ማረጋገጫ፣ ማሳሰቢያ ምልክት የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት የሚያስተላልፍ ዕቃ፣ ሁኔታ ወይም ድርጊት ሊሆን ይችላል * ምልክቶች ቃል ለተገባለት ነገር እንደ ማሳሰቢያ ያገለግላል * ሰማይ ላይ የምናየው ቀስተ ደመና ከእንግዲህ በምድር ሁሉ ላይ በሚሆን ጎርፍ ሕይወትን ሁሉ እንደማያጠፋ የሚያሳስብ ምልክት ነው * ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዲሆን ልጆቻቸውን እንዲገርዙ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ * ምልክቶች አንድን ነገር ይገልጣሉ ወይም ያመለክታሉ * በቤተ ልሔም አዲስ የተወለደው መሲህ የትኛው ሕፃን መሆኑን ማወቅ እንዲችሉ መልአኩ ለእረኞቹ ምልክት ነገራቸው * ማሰር ያለባቸው እርሱን እንደሆነ ለአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ለማሳየት ምልክት እንዲሆን ይሁዳ ኢየሱስን ሳመ * ምልክቶች አንድ ነገር እውነት መሆኑን ሊያመለክቱ ይችላሉ * ነቢያትና ሐዋርያት የደረጓቸው ተአምራት የተናገሩት የእግዚአብሔርን መልእክት መሆኑን የሚያረጋግጡ ምልክቶች ነበሩ * ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት እርሱ በእውነት መሲሕ ለመሆኑ፣ ምልክቶች ናቸው