am_tw/bible/kt/sign.md

14 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ምልክት፥ ማረጋገጫ፣ ማሳሰቢያ
ምልክት የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት የሚያስተላልፍ ዕቃ፣ ሁኔታ ወይም ድርጊት ሊሆን ይችላል
* ምልክቶች ቃል ለተገባለት ነገር እንደ ማሳሰቢያ ያገለግላል
* ሰማይ ላይ የምናየው ቀስተ ደመና ከእንግዲህ በምድር ሁሉ ላይ በሚሆን ጎርፍ ሕይወትን ሁሉ እንደማያጠፋ የሚያሳስብ ምልክት ነው
* ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዲሆን ልጆቻቸውን እንዲገርዙ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ
* ምልክቶች አንድን ነገር ይገልጣሉ ወይም ያመለክታሉ
* በቤተ ልሔም አዲስ የተወለደው መሲህ የትኛው ሕፃን መሆኑን ማወቅ እንዲችሉ መልአኩ ለእረኞቹ ምልክት ነገራቸው
* ማሰር ያለባቸው እርሱን እንደሆነ ለአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ለማሳየት ምልክት እንዲሆን ይሁዳ ኢየሱስን ሳመ
* ምልክቶች አንድ ነገር እውነት መሆኑን ሊያመለክቱ ይችላሉ
* ነቢያትና ሐዋርያት የደረጓቸው ተአምራት የተናገሩት የእግዚአብሔርን መልእክት መሆኑን የሚያረጋግጡ ምልክቶች ነበሩ
* ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት እርሱ በእውነት መሲሕ ለመሆኑ፣ ምልክቶች ናቸው