am_tw/bible/kt/scribe.md

800 B

ጸሐፍት፣ የአይሁድ ሕግ መምሕራን

ጸሐፍት መንግሥታዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሰንዶችን በእጅ ጽሑፍ የማርቀቅ ወይም የመገልበጥ ኅላፊነት የነበረባቸው ባለ ሥልጣኖች ናቸው

  • የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በእጅ መጻፍና ለትውልድ ማቆየት የጸሐፍት ኅላፊነት ነበር
  • ጸሐፍት የእግዚአብሔርን ሕግ የሚመለከቱ አስተሳሰቦችንና ማብራርያዎችን ይጽፉ፣ ይጠብቁና ይተረጉሙ ነበር
  • አልፎ አልፎም ጸሐፍት ሁነኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣኖችም ይሆናሉ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም የሚታወቁ ጸሐፍት ባሮክና ዕዝራ ናቸው