# ጸሐፍት፣ የአይሁድ ሕግ መምሕራን ጸሐፍት መንግሥታዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሰንዶችን በእጅ ጽሑፍ የማርቀቅ ወይም የመገልበጥ ኅላፊነት የነበረባቸው ባለ ሥልጣኖች ናቸው * የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በእጅ መጻፍና ለትውልድ ማቆየት የጸሐፍት ኅላፊነት ነበር * ጸሐፍት የእግዚአብሔርን ሕግ የሚመለከቱ አስተሳሰቦችንና ማብራርያዎችን ይጽፉ፣ ይጠብቁና ይተረጉሙ ነበር * አልፎ አልፎም ጸሐፍት ሁነኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣኖችም ይሆናሉ * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም የሚታወቁ ጸሐፍት ባሮክና ዕዝራ ናቸው