am_tw/bible/kt/sabbath.md

9 lines
873 B
Markdown

# ሰንበት
ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ነው፤ ይህ ቀን ምንም ሥራ የማይሠራበት የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞ ነበር።
* እግዚአብሔር ዓለምን የመፍጠር ሥራውን እንደጨረሰ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ
* በተመሳሳይ መንገድ ሰባተኛውን ቀን የዕረፍትና እርሱ የሚመለክበት የተለየ ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ
* “ሰንበትን መቀደስ” በሁለት ድንጋይ ጽፎ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ዐሥሩ ትእዛዞች አንዱ ነው
* በአይሁድ ቀን አቆጣጠር መሠረት ሰንበት አርብ ፀሐይ ሲጠልቅ ይጀምርና ቅዳሜ ፀሐይ ሲጠልቅ ያበቃል