# ሰንበት ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ነው፤ ይህ ቀን ምንም ሥራ የማይሠራበት የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞ ነበር። * እግዚአብሔር ዓለምን የመፍጠር ሥራውን እንደጨረሰ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ * በተመሳሳይ መንገድ ሰባተኛውን ቀን የዕረፍትና እርሱ የሚመለክበት የተለየ ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ * “ሰንበትን መቀደስ” በሁለት ድንጋይ ጽፎ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ዐሥሩ ትእዛዞች አንዱ ነው * በአይሁድ ቀን አቆጣጠር መሠረት ሰንበት አርብ ፀሐይ ሲጠልቅ ይጀምርና ቅዳሜ ፀሐይ ሲጠልቅ ያበቃል