am_tw/bible/kt/sabbath.md

873 B

ሰንበት

ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ነው፤ ይህ ቀን ምንም ሥራ የማይሠራበት የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞ ነበር።

  • እግዚአብሔር ዓለምን የመፍጠር ሥራውን እንደጨረሰ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ
  • በተመሳሳይ መንገድ ሰባተኛውን ቀን የዕረፍትና እርሱ የሚመለክበት የተለየ ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ
  • “ሰንበትን መቀደስ” በሁለት ድንጋይ ጽፎ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ዐሥሩ ትእዛዞች አንዱ ነው
  • በአይሁድ ቀን አቆጣጠር መሠረት ሰንበት አርብ ፀሐይ ሲጠልቅ ይጀምርና ቅዳሜ ፀሐይ ሲጠልቅ ያበቃል