am_tw/bible/kt/reveal.md

1.2 KiB

መግለጽ፣ መገለጽ (ራእይ)

“መግለጽ” አንድ ነገር እንዲታወቅ ማድረግ ማለት ነው “መገለጽ” እንዲታወቅ የተደረገ ነገር ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ አብዛኛውን ጊዜ “መገለጽ” የሚለው ጥቅም ላይ የዋለው እግዚአብሔር ራሱን ለሕዝቡ ማሳወቁን ለማመልከት ነው።
  • በፈጠረው ፍጥረት ሁሉና በቃልና በጽሑፍ በሰፈሩ መልእክቶች ከሰዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ እግዚአብሔር ራሱን ገልጿል።
  • በሕልምና በራእይም እግዚአብሔር ራሱን ይገለጻል።
  • ወንጌልን የተቀበለው፣ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ባገኘው መገለጥ” እንደ ነበር ጳውሎስ ሲናገር፣ ወንጌልን ግልጽ ያደረገለት ኢየሱስ ራሱ መሆኑን ማመልከቱ ነው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኘው፣ “የዮሐንስ ራእይ” በመጨረሻው ዘመን ስለሚሆኑ ነገሮች እግዚአብሔር ስለ ሰጠው መገለጽ ይናገራል። ለሐዋርያው ዮሐንስ እነዚህን ነገሮች የገለጸው በራእይ ነበር።