# መግለጽ፣ መገለጽ (ራእይ) “መግለጽ” አንድ ነገር እንዲታወቅ ማድረግ ማለት ነው “መገለጽ” እንዲታወቅ የተደረገ ነገር ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ አብዛኛውን ጊዜ “መገለጽ” የሚለው ጥቅም ላይ የዋለው እግዚአብሔር ራሱን ለሕዝቡ ማሳወቁን ለማመልከት ነው። * በፈጠረው ፍጥረት ሁሉና በቃልና በጽሑፍ በሰፈሩ መልእክቶች ከሰዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ እግዚአብሔር ራሱን ገልጿል። * በሕልምና በራእይም እግዚአብሔር ራሱን ይገለጻል። * ወንጌልን የተቀበለው፣ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ባገኘው መገለጥ” እንደ ነበር ጳውሎስ ሲናገር፣ ወንጌልን ግልጽ ያደረገለት ኢየሱስ ራሱ መሆኑን ማመልከቱ ነው። * አዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኘው፣ “የዮሐንስ ራእይ” በመጨረሻው ዘመን ስለሚሆኑ ነገሮች እግዚአብሔር ስለ ሰጠው መገለጽ ይናገራል። ለሐዋርያው ዮሐንስ እነዚህን ነገሮች የገለጸው በራእይ ነበር።