am_tw/bible/kt/reveal.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መግለጽ፣ መገለጽ (ራእይ)
“መግለጽ” አንድ ነገር እንዲታወቅ ማድረግ ማለት ነው “መገለጽ” እንዲታወቅ የተደረገ ነገር ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ አብዛኛውን ጊዜ “መገለጽ” የሚለው ጥቅም ላይ የዋለው እግዚአብሔር ራሱን ለሕዝቡ ማሳወቁን ለማመልከት ነው።
* በፈጠረው ፍጥረት ሁሉና በቃልና በጽሑፍ በሰፈሩ መልእክቶች ከሰዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ እግዚአብሔር ራሱን ገልጿል።
* በሕልምና በራእይም እግዚአብሔር ራሱን ይገለጻል።
* ወንጌልን የተቀበለው፣ “ከኢየሱስ ክርስቶስ ባገኘው መገለጥ” እንደ ነበር ጳውሎስ ሲናገር፣ ወንጌልን ግልጽ ያደረገለት ኢየሱስ ራሱ መሆኑን ማመልከቱ ነው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ የሚገኘው፣ “የዮሐንስ ራእይ” በመጨረሻው ዘመን ስለሚሆኑ ነገሮች እግዚአብሔር ስለ ሰጠው መገለጽ ይናገራል። ለሐዋርያው ዮሐንስ እነዚህን ነገሮች የገለጸው በራእይ ነበር።