am_tw/bible/kt/reconcile.md

8 lines
935 B
Markdown

# ማስታረቅ፣ ዕርቅ
“ማስታረቅ” እና፣ “ዕርቅ” ቀድሞ እርስ በርስ ይጠላሉ በነበሩ ሰዎች መካከል፣ “ሰላም ማድረግ” ማለት ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት እግዚአብሔር ሰዎችን ከራሱ ጋር ማስታረቁን ያመለክታል።
* በኀጢአት ምክንያት የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ነበር። ከፍቅርና ርኅራኄው የተነሣ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ሰዎች ከእርሱ ጋር የሚታረቁበትን መንገድ አዘጋጀ።
* የኢየሱስ መሥዋዕት ለኀጢአታችን የተከፈለ ዋጋ መሆኑን በማመን ሰዎች ይቅርታን አግኝተው ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖራቸዋል።