am_tw/bible/kt/reconcile.md

935 B

ማስታረቅ፣ ዕርቅ

“ማስታረቅ” እና፣ “ዕርቅ” ቀድሞ እርስ በርስ ይጠላሉ በነበሩ ሰዎች መካከል፣ “ሰላም ማድረግ” ማለት ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት እግዚአብሔር ሰዎችን ከራሱ ጋር ማስታረቁን ያመለክታል።
  • በኀጢአት ምክንያት የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ነበር። ከፍቅርና ርኅራኄው የተነሣ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ሰዎች ከእርሱ ጋር የሚታረቁበትን መንገድ አዘጋጀ።
  • የኢየሱስ መሥዋዕት ለኀጢአታችን የተከፈለ ዋጋ መሆኑን በማመን ሰዎች ይቅርታን አግኝተው ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖራቸዋል።